ዳግም ንባብ በአልወለድም

  • አንተነህ አወቀ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ፣ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ - አማርኛ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር
Keywords: መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቁምታ፣ ሀዲስ ታሪካዊ፣ በይነ አሀድ፣ በይነ ዲስፕሊን

Abstract

የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነው አልወለድም የበርካታ ጥናቶችና የሥነጽሑፍ መድረኮች መወያያ ጉዳይ የነበረና ያለ ሲሆን፣ ይህ ጥናት ግን ለየት ባለ መልኩ በልቦለዱ ላይ ትንታኔ ለማድረግ የሞከረ ነው፡፡ ትንታኔው የተደረገው ሀዲስ ታሪካዊ ሂስን እንደማዕቀፍ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከታሪክ ሰነድና ከደራሲው የህይወት ታሪክ ጋር በማዛመድ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የደራሲው፣ የድርሰቱና ድርሰቱ የታተመበት ዘመን ማህበራዊ ፖለቲካዊ አውዶችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ በትንተናውም መሰረት አቤ ጉበኛ የሀገሪቱን ሁኔታ በልቦለዱ ሲገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስን፣ የአክአብና ሎዊ ታሪክን፣ ምሳሌ እንደአደረገ፣ የልቦለዱ መቼት፣ ኢይዝራኤሎስ፣ የአክአብና ኤልዛቤል ግዛት ከሆነው ኢይዝራኤል/እስራኤል እንደተወሰደ፣ የአክአብ መንግስት በኢዩ እንደተወረሰ ሁሉ በልቦለዱም የነሙሴ ገራቢዶስ ፊዩዳላዊ መንግሥት በወታደራዊው መንግሥት በማርሻል ጃፌሮስ እንደተገለበጠ፣ እነዚህ ደግሞ በጥቅሉ የኃይለሥላሴን መንግሥት አስተዳደር እንዳሳዩ እና የወታደራዊውን መፈንቅለ መንግሥት እንደተነበዩ 3፤ አቀንቃኙ ገጸ ባህሪ አንዳንድ የክርስቶስን ባህሪያት እንደተጋራ መረዳት ተችሏል፡፡ ደራሲውም ከአቀንቃኙ ገጸ ባህሪ መምህርነቱን፣ የለውጥ አርአያነቱን፣ መስዋዕትነቱን፣ ከክርስቶስም የእውነት መምህርነቱንና መስዋዕትነቱን ተጋርቶታል ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ ደራሲው በዚህ መልክ ለመጻፍ የቻለው አንድም የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ በማወቁ ሲሆን በስልት ረገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ምሳሌ መጻፉ ደግሞ የኃይማኖት ትምህርት እወቀቱን በመጠቀሙ ነው፡፡ ከዚህም ደራሲና ድርሰት በዘመኑ ባህል፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሥርዓት እንደሚቀረጹ ሁሉ በተቃራኒው ደራሲውም ሆነ ድርሰቱ ዘመኑን በመቅረጽ ረገድ የሚጫወቱት ሚና መኖሩን መገንዘብ እንችላለን፡፡

References

ሀዲስ ዓለማየሁ (1982) ፍቅር እስከ መቃብር (7ኛ እትም)፡፡ አዲስ አበባ፡፡ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት፡፡

መስፍን ማሞ (ቀን የለውም)፡፡ አልወለድም፡ አስተያየት: Retrieved from Ethiopiazare.files.wordpress.

በሪሁን ከበደ (1992)፡፡ የኃይለሥላሴ ታሪክ፡፡ አዲስ አበባ፡፡ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡

አሽኔ ጌታቸው (2001) ፍልሚያ፡፡ አዳማ፡፡ እድር ማተሚያ ቤት፡፡

አቤ ጉበኛ (1993)፡፡ አልወለድም (2ኛ እትም)፡፡ አዲስ አበባ፡፡ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡፡

ኤልያስ አያልነህ (1991)፡፡ የአቤ ጉበኛ ብዕራዊ ተጋድሎ፡፡ አዲስ አበባ፡፡ ብራና ማተሚያ ቤት፡፡

የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማበህበር (1992)፡፡ የመጽሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት (6ኛ እትም)፡፡አዲስ አበባ፡፡ ባናዊ ማተሚያ ቤት፡፡

Bahru Zewde (2002). A History of Modern Ethiopia: 1855-1991 (2nd ed.). Addis Ababa: Addis Ababa University Press.

Bertens, H. (2001). Literary Theory: The Basics. London: Routledge.

Doğan, E. (2005). New Historicism and Renaissance Culture. Ankara Üniversitesi Dilve Tarih-Coğrafya Fakültesi Dergisi, 45(1), 77-95. Retrieved from www19.homepage.villanova.edu/silvia.nagyzekmi/teoria2010/

Fikre Tollossa (1983). Realism and Amharic Literature (1908 -1981).

Disserttion, der Universitat Breman, Beman.

Ghirmai Negash (1995). Literature and Politics in Ethiopia: A case Study of Abe Gubenya’s Alwellwdim. In Tadesse Adera and Ali Jemale (eds.) Silence is not Golden:a Critical Anthology of Ethiopian Literature (pp. 135-153) Lawrenceville: The Red Sea Press Inc.

Hawthorn, J. (1992). Studying the Novel: An Introduction. London: Hadder Arnold.

Holub, R. (1992). New Historicism and the New World Order: The Politics of Textuality and Power in German Studies. Monatshefte, 84(2), 171-182.

Kane, T. L. (1975). Ethiopian Literature in Amharic. Germany: Otto Harrassowizt.

Molvaer, R. K (1997). The Creative Lives of Modern Ethiopia’s literary Giants and Pioneers. Asmara: The Red Sea Press, Inc.

Tesfaye Dagnew (1986) ‹‹ The Portrayal of Society and the Concept of Modernization in Abbe Gobegna's Novels ›› MA Thesis, 71 Addis Ababa University.

Tyson, L.(2006). Critical Theory Today: A User-Friendly Guide. 2 ed. U.S.A: Routledge, Taylor and Francis Group.

Zekiye, ER (n.d.).Tom Stoppard’s Arcadia: A Postmodernist/ New historicist Reading of the Play. Retrieved from http://Dargiler.ankara.edu.tr/Dargiler/13/190/1469.pdf.

Published
2022-04-12
Section
Articles